✦
ጠቅላላ
•General
ዘይክል ኩሎ
Lyrics
ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር
አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን ንህነ አበከ
ተማህፃነ
የድሆች አለኝታ ተስፋ ላጡ ተስፋ ሁሉን
የምትችል ደራሽ ለተገፉ
ለእኛም ድረስልን በኃጢያት ሣንጠፋ
ናዛዜ ኅዙናን
ከገነት ሲባረር አዳም ተሳስቶ
ባለወሰ ጊዜ ልጅነቱን አጥቶ
ትድናለህ ብለህ ያዳንከው በመስቀል
የቅዱሳን አምላክ አቤቱ ቸል አትበል
ወተስፋ ቅዱሳን
ሕዝበ እስራኤልን ፈርዖን ሲመራቸው
ጭንቅና መከራ እያፀናባቸው
በነራሔል ልቅሶ ሙሴን ላክላቸው
ረዳኤ ምንዱባን
እኛም ወገኖችህ ወዳንተ እንጮሃለን
ከጭንቅ ከመከራ እንድትታደገን
ጌታ አንተ ነህናናዛዜ ኅዙናን
ናዛዜ ኅዙናን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.