✦
ጠቅላላ
•General
በሰርጋችን ዕለት
Lyrics
በሰርጋችን ዕለት እንድትባርከን
ጌታ ጠርተንሀል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋራ ና ከእመቤታችን
ከመላዕክት ጋራ ና በሰርጋችን
ከሐዋርያት ጋራ ና በሰርጋችን
ከወዳጆህ ጋራ ና በሰርጋችን
በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ስንጠራህ
ስለእናትህ ብለህ ጌታችን እንዳትቀር
አንተ ነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ
በረከት የሱ ነው ቤታችንን ይሙላ
በጎደለው ሁሉ እየጨመርሽልን
ቤታችን ሁሉ ሙይው እናታችንን
ለአገልጋዮቹም ድንግል ንገሪያቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙላቸው
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.