✦
ጠቅላላ
•General
ደመቀ አበራልን
Lyrics
ደመቀ አበራልን የአማኤል ስራ/2/
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሳራ
በቤተክርስቲያን ጥላ ተጠልለው
ተክሊል አድርገዋል መሽሪት መሽራው
ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው
ሙሽሪት ሙሽራው አበራ ገፃቸው
የተራራቀ አካል አንድ ሆነ በተክሊል
እግዚአብሔር ይመስገን እልል እልል እንበል
አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ
አዳም የሰበከው ይኸው ዛሬ ታየ
የተክሊል ብርሃኗ በኛ መሀል በርቶ
ረቂቅ አንድነት ታየ በእርሷ ጎልቶ
ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን
ምስጢሩን የሚገልፅ እግዚአብሔር ይመስገን
ነጭ መጎናፀፊያ በአንድ ተጎናፅፈው
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አረፉ በጥላው
ሙሽሪት መሽራው ለፍቅር ተሸነፉ
ለቁርባ መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.