ጠቅላላ

General

የቃናው ደስታ

Lyrics

የቃናው ደስታ ዛሬ ተደገመ

ጌታ ከእናቱ ጋር በሰርጉ ታደመ

የዘለዓለም አምላክ ስላለ በዚህ ቤት

ሙሽራው ሙሽሪት አገኙ በረከት

አ.ዝ

መርዓት ተሸልማ የድንግልና አክሊል

እዩት ስርዓቱን እጅግ ያስደስታል

አንድ አካል ሙሽሮች እዪቸው ሲያበሩ

በወንጌሉ በተክሊሉ ሄዱ እየተመሩ

እንግዳቸው ብዙ ድንኳናቸው ሙሉ

ጌታ ከእናቱ ጋር አለ በመሀሉ

የወይን ጋኖቹ ዛሬ ሙሉ ናቸው

አማኑኤል ድንግል ማርያም ስላሉ ቤታቸው

አ.ዝ

አ.ዝ

በክብር ታጅቦ ሲወጣ መርዓዊ

እጅግ ያስደስታል አይደለም ምድራዊ

ዛሬም በዚህ ድንኳን ደስታ ተደረገ

በዓማኑኤል በአምላካቸው ስለተባረከ

በተክሊል በቁርባን የሆነው አንድነት

አይነጣጠልም ዳግም ወደ ሁለት

ሙሽሪት ሙሽራው ተደሰቱ ዛሬ

በሰርጋቸው ተገለጠ የእምነታቸው ፍሬ

አ.ዝ

በቃና ዘገሊላ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening