✦
ጠቅላላ
•General
ሁለቱም አንድ ሆኑ
Lyrics
ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ/2/
በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ
ሁለቱም አንድ ሆኑ
አ.ዝ
ወንድና ሴት አርጎ ስለፈጠራቸው
በኋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው
እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል
ከሚስቱም ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል
ሁለቱም አንድ ስጋ ሆነው ይኖራሉ
ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ
አንድ ስጋ ናቸው አይደሉም ሁለት
የባልና የሚስት ሕይወት ወደፊት
አ.ዝ
አ.ዝ
ከእንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራቸው
በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያቸው
ለወገኖቻችሁ ምሳሌ ሆናችሁ
በክርስትና ፍቅር አምላክ ያቁማችሁ
ምንጣፋቸው ቡሩክ መኝታችሁ ንጹህ
ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
ዓለም እንዲደነቅ ጠላት እንዲያፍር
በሐዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር
አ.ዝ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.