ጠቅላላ

General

ንጽሒት ቅድስት

Lyrics

ንጽሒት ቅድስት ቡርክት

የአምላክ እናት እመቤት

ልጆችህ ሙሽሮች ሁለቱም አንድ ሆኑ

ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ/2/

ፍፁም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር

አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር

መሰረቱ ዛሬ ልጆችሽ

አ.ዝ

ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሸ

ድንግል ጎጆቸውን ቀድሰሽ

እውነተኛ ፍቅር መስርተሽ

በመካከላቸው ተገኝተሽ

ሁሉን አሰጫቸው አማልደሽ

አ.ዝ

አ.ዝ

ሙሽሮቹም አምነው በምልጃሽ

እናታችን ባርኪን ነይ ሲሉሽ

ፈጥነሽ ድረሺና በሰርጋቸው

ነይ ተመላለሺ መሀላቸው

አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ

የህይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ

ሙሽሮቹ ዛሬም ይጠሩሻል

የጎጆአችን ፋና ነይ ይሉሻል

አ.ዝ

አ.ዝ

ቃና ዘገሊላ ተገኝተሸ

መልካሙን ጋብቻ ያስባረክሽ

ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሰርጋቸው

ነይ ተመላለሺ መሀላቸው

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening