ጠቅላላ

General

ቃና ዘገሊላ

Lyrics

ቃና ዘገሊላ/2/ በዚያ በሰርግ ቤት

ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ

ተገኝተሀል ጌታ ከእናትህ ጋራ

አ.ዝ

እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙበት

ሲበሉ ሰጠጡ ወይኑ አልቆበት

ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም

አንቺ ደረሽለት ሆንሽው አማላጅ

አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው

ሁሉ ይቻልሀል ወይኑን ሙላላቸው

ማድጋው ባዶነው ብለሽ የተናገርሽ

ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ

አ.ዝ

የጌታ አምላክነት የተገለፀበት

ምነኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት

ዛሬ ይኸው በዚህ በሰርገኞቹ ቤት

በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት

አ.ዝ

ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን

በቃና ገሊላ ሁላችን አየን

እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን

ሁሌም ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening