ጠቅላላ

General

አጅቡት በእልልታ

Lyrics

አጅቡት በእልልታ ሲመጣ ሙሽራው

ፍፁም የሚያስደስት የሰርጉ እለት ነው

ዘመዶቹ ሁሉ ተቀበሉ ውጡ

የሙሽራው መምጫ አሁን ነው ሰዓቱ

እልል/2/ እንበል እንዘምር በእልልታ

ይህን ላደረገ ለሠራዊት ጌታ

ሁሉንም በጊዜው ይፈፅማልና

ይኸው አበቃችሁ ለዚህ መልካም ዜና

አ.ዝ

ሙሽሪት ተደሰች ዝምታው ምንድን ነው

የዳግም ልደትሽ የሰርግሽ እለት ነው

አዳም ጎንሽ ቆሞ ሔዋን ሆይ ሲልሽ

መንፈሳዊ ሀሴት ይሙላ በልብሽ

እህት ወንድሞቿ እናትና አባቷ

ተነሱ ዘምሩ በልጃችሁ ደስታ

መግቢያዋ ነውና ወደ ቤቷ ዛሬ

ወደ አዲስ ጎጆዋ ሸኟት በዝማሬ

አ.ዝ

አ.ዝ

ቤተሰቦችሽን ሁሉንም ትተሽ

መሄድሽ ነውና ወደ መኖሪያሽ

ከአማኑኤል ጋራ ባልሽን ይዘሽ

ተነሽ ሙሽራዬ ደርሷል ሰዓትሽ

ከድንግል ማርያም ጋር ሚስትህን ይዘህ

ተነስ ወንድሜ ሆይ ደርሷል ሰዓትህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening