ጠቅላላ
•General
ዘወይን
ዘወይን /2/ ቤተ ቃና ዘወይን/4/
ቤተ ቃና ዘወይን/2/
አ.ዝ
በቃናዋ መንደር ዘወይን
ሰርግ ተደግሶ ዘወይን
ወይኑ ተሰናድቶ ዘወይን
ዳሱ ተቀልሶ ዘወይን
ዶኪማስም ጠራ ዘወይን
ደቀ መዛሙርቱን ዘወይን
ኢየሱስን እና ዘወይን
ማርያም እናቱን ዘወይን
ሲበሉ ሲጠጡ ዘወይን
እጅግ ደስ አላቸው ዘወይን
ያ መናኛ ወይን ዘወይን
እየጣፈጣቸው ዘወይን
እልልታውም ደምቋል ዘወይን
ሙሽራውም ኮርቷል ዘወይን
ሰርጉ ለእንግዶቹ ዘወይን
የበቃ መስሎታል ዘወይን
አ.ዝ
ወይኑ በመካከል ዘወይን
አለቀ ከጋኑ ዘወይን
አፍረው ተደበቁ ዘወይን
አሳላፊው ሁሉ ዘወይን
ማንም ሰው ሰይነግራት ዘወይን
ይህንን ተረድታ ዘወይን
ድንግል ልታማልድ ዘወይን
ሔደች ወደ ጌታ ዘወይን
አ.ዝ
ጋኖቹን ሙሏቸው ዘወይን
ውኃውን ቀድታችሁ ዘወይን
ብሏችኋል ልጄ ዘወይን
ታዘዙ ታምናችሁ ዘወይን
ብላ ስትናገር ዘወይን
ለአሳላፊዎቹ ዘወይን
አምነው ጓዳ ገቡ ዘወይን
ተሞሉ ጋኖቹ ዘወይን
አ.ዝ
አ.ዝ
ማድጋው ሲከፈት ዘወይን
መልካም ወይን ሆነ ዘወይን
የክርስቶስ ክብር ዘወይን
በቤቱ ገነነ ዘወይን
የእመ አምላክ ፀሎት ዘወይን
ታሪኩን ቀየረ ዘወይን
መናኛው በሀዲስ ዘወይን
ይኸው ተቀየረ ዘወይን
ዛሬም ለደከሙ ዘወይን
አልጫ ለሆኑ ዘወይን
የነፍሳቸው ጣፋጭ ዘወይን
አልቆባቸው ወይኑ ዘወይን
ድንግል ትቆማለች ዘወይን
ስለእነርሱ ተግታ ዘወይን
እንዲጣፍጡላት ዘወይን
ለምና ከጌታ ዘወይን
አ.ዝ
አ.ዝ
ልጇም ኤልሻዳይ ነው /2/
ሁሉን አዲስ አርጓል
ጨለማውን ገልጧል
መራሩን አጣፍጧል
ሁሉን ደንቅ አድራጊ
ዛሬም ታምረኛ
ጋኖቹን እንጠብ
እንመለስ እኛ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.