ጠቅላላ

General

እፁብ ድንቅ ሥራ

Lyrics

እፁብ ድንቅ ሥራ/2/

በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ

በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ

ነፍሳችሁ በሰማይ ርግብ ትመስላለች

ከመላዐክት ጋራ ዛሬ ዘምራለች/2/

እልል/2/ በሉ ክርስቲያኖች ሁሉ

ያበራ ጀመረ ሙሽራው ፀዳሉ

ያበራ ጀመረ ሙሽሪት ፀዳሏ

አ.ዝ

ከክርስቶስ ሰላም እንዴት ይርቃል ሰው

ሥጋውና ደሙን ሳይሳሳ ከሰጠው/2/

የመንፈስ ቅዱስ ሕፃናት በመሆን

በሥጋ ወደሙ መቀደስ አለብን/2/

አ.ዝ

አ.ዝ

በእግዚአብሔር ተማርኮ የመኖር ምሥጢር

የዘለዓለም ህይወት ያሰጣል ፍቅር/2/

ሥጋውን ፍሪዳ ደሙን መጠጥ አርጎ

ሰጥቶናል አማኑኤል ሕይወቱን ሰውቶ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening