ጠቅላላ

General

ድንቅነው በጣም

Lyrics

ድንቅነው በጣም ድንቅ ነው

በሰርጋችሁ እለት ተገኘ መድሃኒዓለም

በሰርጋችሁ እለት ተገኘች ድንግል ማርያም

በቃልህ ተመርተው ለዚህ ቀን ደርሰዋል

በፊትህ ጋብቻን ይኸው መስርተዋል

በአፈሰስከው ደምህ ህብረት መስርተዋል

በስጋም በነፍስም/2/ ያንተ ነን ብለዋል

አ.ዝ

ከአዳም አንድ አጥንት ከጎኑ ወስደህ

አጋር እንድትሆነው ሔዋንን ሰራህ

ሁለቱንም ባርከህ እንደቀደስካቸው

ዛሬም ለሙሽሮች/2/ ፀጋህን ስጣቸው

አ.ዝ

አ.ዝ

ጌታ ሆይ በህግህ በቃልህ መሰረት

አንድ ሆነዋልና በዚች ቅድስት እለት

እርሱንም እርሷንም ባርክ ቀድሳቸው

ዘለዓለማዊ ክብር /2/ ፀጋህን ስጣቸው

የዲያቢሎስ ተንኮል እንዳያጠምዳቸው

እስከ መጨረሻው ጋሻ ሁንላቸው

ከቅድስቲቷ ቤት ሁለቱም ሳይርቁ

ጽናቱን ስጣቸው/2/ አብረው እንዲዘልቁ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening