ጠቅላላ

General

ወንድና ሴት

Lyrics

ወንድና ሴት አርጎ ስለፈጠራቸው

ኋላም ለኑሮአቸው ጋብቻን ሰጣቸው

አንዴ ከተጋቡ አንድ ስጋ ናቸው

ከእንግዲህ ወደፊት ይፀናል ፍቅራቸው

ደስ ይበለን ሙሽሪት መሽራው/2/

አንድ አካል ሆነዋል አምላክ አጣምሯቸው

በምንም ምክንያት ምንም አይለያቸው

በጣም ይወዳታል ባል ክብርት ሚስቱን

ስለሷ አሳልፎ ይሰጣል ነፍሱን

አ.ዝ

ለአብርሃም ለሣራ እንደሰጠ ትዳር

ለእናንተም ይለግስ የዘልዓለም ፍቅር

አንቺም እንደ ሣራ እርሱም እንደአብርሃም

ተፋቅራችሁ ኑሩ እስከ ዘለዓለም

አ.ዝ

አ.ዝ

ለዚህ ላበቃችሁ ለቸሩ አምላካችን

ምስጋና ይድረሰው ዛሬ ከሁላችን

በሉ ደህና ግቡ ወደ አዲስ ጎጆአችሁ

አምላክ በጥበቡ ፍቅርን ያላብሳችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening