✦
ጠቅላላ
•General
ሙሽሮች
Lyrics
ሙሽሮች አንኳን ደስ አላችሁ/2/
ለዚህ ቀን ይኸው ደረሳችሁ
በአምላክ ፊት እጅግ ከበራችሁ
በእግዚአብሔር ቸርነት በመልካም ፈቃዱ
በቅዱስ ቁርባኑ ዛሬ ተዋሀዱ/2/
በስርዐተ ተክሊል በስጋ ወደሙ
በመድሀኒዓለም ፊት ጋብቻን ፈፀሙ
በቤተክርስቲያን በፈጣሪያቸው ፊት
ሁለቱም አንድ ሆኑ በዚህ ቅዱስ እለት/2/
አንድ የሚያደርጋቸው ተነቦ ወንጌሉ
በካህኑ መስቀል በረከት ታደሉ/2/
አ.ዝ
በወንጌል ትዕዛዝ በሐዋርያት ቃል
በእመብርሃን ፊት ጋብቻቸው ፀድቋል/2/
በአምላክ ስጋና ደም ሁለቱም ታተሙ
የሕብረት ቃል ኪዳን በአንድ ላይ አሰሙ/2/
ፀንቶ የሚያፀና የማይለያያቸው
ክቡር ቃል ስላለ በመካከላቸው/2/
እስከ መጨረሻው አንድ አካል ሆነዋል
የአማኑኤል ስጋ አስተሳስሮአቸዋል/2/
አ.ዝ
እግሮቻችሁ ይገስግሱ ወደ እውነት/2/
አማናዊው ማዕድ ክርስቶስ ወደ አለበት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.