ጠቅላላ

General

የምስራች

Lyrics

የምስራች ደስ ይበላችሁ/2/

አሸብርቆ ዋለ ሙሽሮች ሰርጋችሁ/2/

አ.ዝ

ህይወታችሁ ሰላማዊ ፍጹም ፍቅር/2/

እንደ ጽጌሬዳ እንደ አደይ ፈክቶ እንዲኖር

አማኑኤል ያርገው ፍፁም ትስስር

መተሳሰብ መከባበር ይሁን ግብራችሁ/2/

ሰርጎ እንዳይገባ ዲያቢሎስ በመሀላችሁ

በጾም ፀሎት ይታሰር ሙሽሮች ጎጆአችሁ

አ.ዝ

እግሮቻችሁ ይገስግሱ ወደ እውነት/2/

አማናዊው ማዕድ ክርስቶስ ወደ አለበት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening