✦
ጠቅላላ
•General
ሙሽራዬ
Lyrics
ሙሽራዬ/3/ አበባዬ/2/
አ.ዝ
ከጎንህ የምትሆን እህት አገኘህ
የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለህ
እግዚአብሔር ፈቅዶ ለዚህ ካበቃችሁ
ቤታችሁ ይመረቅ በፍቅር ያፅናችሁ
ወንድም አግኝተሻል የሚያስብልሽ
የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለሽ
እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ደስ ብሎናል
በቤተክርስቲያን ሰርጋችሁ ውብ ሆኗል
አ.ዝ
እንደ ነፍስህ አርገህ እንድትወዳት
አደራ ሰጠንህ በጌታችን ፊት
እንድታስቢለት አንቺም ለአካልሽ
አደራ ትላለች ወንጌል እናትሽ
በስጋ ወደሙ ሕይወት አግኝታችሁ
ፍሬአችሁም ይብዛ ይባረክ ጓዳችሁ
አምላክ ያለበት ነው ይሄ ጋብቻችሁ
እስከ መጨረሻው ኑሩ ደስ ብሎአችሁ
አ.ዝ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.