ጠቅላላ

General

እስመ ለዓለም

Lyrics

እስመ ለዓለም ኧኸ እስመ ለዓለም

ለዓለም ለዓለም እስመ ለዓለም/2/ በሉላቸው

ደስ ይበልን በጣም ኧኸ አይግባን ፍራቻ ኧኸ

ጌታ ባርኮልናል ኧኸ ቅዱሱን ጋብቻ ኧኸ

ቃና ዘገሊላ ኧኸ ከእናቱ ጋር ገብቶ ኧኸ

ውኃውን ለወጠ ኧኸ ወደ ወይን አሳክቶ ኧኸ

አ.ዝ

ሙሽራው መልካም ነው ኧኸ ሙሽሪት መልካም

ኧኸ

ጋብቻችሁ ይመር ኧኸ በዓለም ይዳረስ ኧኸ

ይነገር ስብከቱ ኧኸ ጽፎታል ጳውሎስ ኧኸ

ዳዊትም ይጠራ ኧኸ በገና ይደርድር ኧኸ

በመዝሙር ይፈክር ኧኸ ትንቢትን ይናገር

ኧኸ

መድሀኒዓለም ይምጣ ኧኸ ይሰራ ጥበቡን ኧኸ

በግብዣችሁ ጥሯት ኧኸ ድንግል ማርያምን

ኧኸ

ሐዋርያት ይምጡ ኧኸ ጻድቃንም ይጠሩ ኧኸ

ጋብቻችሁ ይመር ኧኸ መልካም ፍሬን አፍሩ

ኧኸ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening