✦
ጠቅላላ
•General
ንሴብሆ ለሥላሴ
Lyrics
ንሴብሆ ለሥላሴ/4/
ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ/4/
የእኛ አማላጅ እናታችን/4/
ነይ ነይ ወደኛ እመቤታችን ገ /2/
ና ወደኛ ሚካኤል/4/
መልዐከ ምክሩ ለልዑል
ከእግራችን ይውደቅ ሣጥናኤል ] /2/
ና ወደኛ ገብርኤል/4/
ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል
በክንፍህ ጥላ እንጠለል
}/2/
ና ወደኛ ዑራኤል/4/
እንደ ቅዱስ ዕዝራ ሱቱኤል
ጥበብን ሥጠን ማስተዋል ∫
}/2/
ና ወደኛ በፈረስ/4/
የልዳው ፀሐይ ጊዮርጊስ
ገድልህን ሰምተን እንፈወስ
}/2/
ና ወደኛ ተክለ ሃይማኖት/4ሇ
እንዲጠብቀን ያንተ ፀሎት
ፀንተን እንድንቆም በሃይማኖት } /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.