✦
ጠቅላላ
•General
የሐብከ ዮም
Lyrics
የሐብከ ዮም የሐብከ መድሀኒዓለም/2/
እድሜ ማቱሳላ ወአብርሃም/2/
ይስጣችሁ ዛሬ ይስጣችሁ መድሀኒዓለም/2/
እድሜ ማቱሳላ የአብርሃም/2/
በቅዱስ ጋብቻ ሙሽሮች የተወሰናችሁ/2/
ክርስቶስ ተገኝቷል በመካከላችሁ/2/
አ.ዝ
የድንጋዮቹን ጋን ወይን ወይን ሊሞላበት/2/
ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቷል በዚህ ቤት/2/
አ.ዝ
ደስታውን አይቶ አምላክ ፍፁም ተደስቷል
ሊባርካችሁም እጆቹን ዘርግቷል
አ.ዝ
በሕይወታችሁ ውስጥ ፍቅር ፍቅር ቅመም ሆኖ/2/
ትሕትናን ይስጣችሁ እግዚአብሔር በቶሎ/2/
አ.ዝ
ሰርጋችሁ እንዲሆን ደስታ ፍቅር የሞላበት/2/
በሕይወታችሁ ውስጥ ክርስቶስ ይግባበት
በሕይወታችሁ ውስጥ አምላክ ይኑርበት
የበረከት ፍሬ በፀጋው እንዲበዛላችሁ/2/
ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ/2/
አ.ዝ
እራስን በመግዛት እውቀት/2/ ለመላችሁ/2/
ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ/2/
በስጋ ወደሙ እግዚአብሔር ስለመረጣችሁ/2/
የመንፈስ ቅዱስ ሕፃናት ናችሁ/2/
አ.ዝ
] /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.