ጠቅላላ

General

ይህን ላደረገ

Lyrics

ይህን ላደረገ ሃሌ ሉያ በሉ/2/

እግዚአብሔር ታማኝ ነው ሁል ጊዜ በቃሉ

ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ ያላችሁ

የያዕቆብ አምላክ ሞገስ ሆነላችሁ

ስንቱን ተራራ አልፈነዋል

በሰገነት ላይ አቁሞናል

እስቲ እንዘምር በደስታ

አ.ዝ

ሁሌም ታማኝ ነው የእኛ ጌታ

ከእኛ የሆነ ምንም የለም

ተመስገን ጌታ ለዘለዓለም

ስራህ አበራ በምስጋና

በሙሽሮች ላይ እንደገና

የማይሆን መስሎ የታየን

በእግዚአብሔር ሆኖ ስላየን

እንደ አሳፍ ልጆች ተሰለፍን

ስሙን በቅኔ ለማመስገን

የተባረከ በመዳፉ

ቅኔን ያፈሳል ሁሌ በአፉ

ከመላዕክት ጋራ አንድ ሆነናል

የእግዚአብሔር ስራ መስጦናል

አ.ዝ

ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ

ያስባል ጌታ ለወዳጁ

መናኛ ይውጣ ከቤታችን

አዲስ እንጠጣ ጌታን ይዘን

አቤኔዘር ነው መዝሙራችን

እየረዳን ነው አምላካችን

ፊታችን በራ በደስታ

ውበት ሆኖናል የእኛ ጌታ

}/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening