ጠቅላላ

General

የኢቲሣ አንበሣ

Lyrics

የኢቲሣ አንበሣ ተክልዬ ተነሣ

ወገንክን ታደገው ከኃጢያት አበሣ

ተኩላወ ለምድ ለብሶ በእርግጥ መጥቷልና

ጴጥሮስ ሆይ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ፅና

ዩሀንስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ፅና

አ.ዝ

የዓለም ምናምንቴ የተባለውመ ቅዱ

የዋሁ መነኩሴ አባ ሕርያቆስ

ቅዳሴ ማርያምን ናና ዛሬ ቅድስ

በእጣኑ መዓዛ ድውያንን ፈውስ/2/

የወንጌል አርበኛ ጎርጎርስ ፍጠን

ምሰሶው ሳይወድቅ መንጋው ሣይበተን

መብረቁ አትናቴዎስ ሞገዱን ገስፀው

ጉባኤያችንንም በመስቀልህ ባርከው/2/

አ.ዝ

መርከቧን የሚያውክ ነፋስ ነፍሷልና

አምላካችን ፈጥነህ አድነን ቶሎ ና

ጴጥሮስ ሆይ ቀስቅሰው ልንጠፋነው ብለህ

ሞገዱ እያየለ ዝም እንዳይል ጌታ/2/

ከሣቴ ብርሃን ሠላማ ቶሎና

ኖላዊ እረኛ ያስፈልጋልና

ስጋውን የጎዳ ነፍሱን የጠቀመ

ንቅ ጉድፍ የሌለው ግብሩ የታረመ/2/

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening