ጠቅላላ

General

ገድሉ ታምራቱ

Lyrics

ገድሉ ታምራቱ እጅግ ብዙ ነው

ጣዖትን አዋርዶ የተሸለመው

የተዋህዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ

አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ

አ.ዝ

ዳግማዊ ዩሀንስ ጠፍር የታጠቀ

ብፁዕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ

የፀጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ

በደብረ ሊባኖስ መናኛ አስከተለ

ደካማ መስሏቸው ባንድ እግሩ ቢያዩት

ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኔ አባት

እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ

ሌጊዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ

አ.ዝ

ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክልዬ

መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለ ሃይማኖት

ወልድ ዋድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት

የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት

ጥላህ ያረፈበት ሆኗል ፀበል ዕምነት

ኑ እና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ

ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening