ጠቅላላ

General

የቅዱሳን በዓት

Lyrics

ልቡና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ

ህሊናን ይገዛል ድጓዝማሬዋ

የቅዱሳን በዓት የፀሎት ዋሻቸው

ቤተክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው

ይዘምሩባታል በአንድነት ተባብረው

የሌዋዊው በትር ፅናፅል ከበሮው

አ.ዝ

የመላዕክት ዜማ የአርያም ዝማሬ

የሚነገርባት የቅዱሳን ፍሬ

የገድላቸው ታምር መንቦግቦጊያው መቅረዝ

የሰማዕታት አክሊል የስራቸው ደሞዝ

አ.ዝ

ከኃጢያት ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ

የቅዱሣን በዓት ልትሆነኝ አገሬ

አ.ዝ

መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው

ይፈውሳልና ተረፈ አፅማቸው

የቅዱሳን በዓት የፀሎት ዋሻቸው

ቤተክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening