ጠቅላላ

General

የፃድቅ ሰው ፀሎት

Lyrics

የፃድቅ ሰው ፀሎት ያድናል/2/

የነፍስን ቁስል ይጠግናል/2/

አ.ዝ

የፍቅር እመቤት ቤዛዊተ ዓለም

ለልጅሽ አሳስቢ በደላችንን

ስለቃልኪዳኑ በቃሉ መሐላ

ልመናሽን ሰምቶ አይለንም ችላ

ገብረ መንፈስ ቅዱ ፃድቁ አባታችን

ረድኤት በረከትህ ይድረስ ለሁላችን

አባ ተክለ ሃይማኖት መቁጠሪያህን አንሳ

ለምን ለልጆችህ እንዳናይ አበሳ

አ.ዝ

የእግዚአብሔር ወዳጅ ገብረ ክርስቶስ

ልመናህ ፀሎትህ መድሃኒት ለነፍስ

ፍቅርህ አይለየን ቂርቆስ ሆይ አደራ

ነፍሳችን እንድትድን ከሢዖል መከራ

ፀሎቷ ደረሰ የክርስቶ ሠምራ

የእግዚአብሔርን ልብ አንኳኩቶ ሊያራራ

ያቺ ቅድስት እናት ሰማዕቷ አርሴማ

ለምና አስገባችን ከፃድቃን ከተማ

አ.ዝ

አባ ሐብተ ማርያም የብርሃን አምሳል

በፀሎት አስበመን ወድቀን እንዳንዝል

ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት ሁላችሁ

ዘወትር አይለየን ፀሎት ልመናችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening