ጠቅላላ

General

ኦ ፍጡነ ረድኤት

Lyrics

ኦ ፍጡነ ረድኤት /2/

የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሠማዕት

ሰላም ላንተ ይሁን ፍጡነ ረድኤት

የልዳው ፀሐይ

/2/

በጨካኝ ንጉስ ፊት ቆምክ አደባባይ

ታማኝ አገልጋይ ነህ ፍጡነ ረድኤት

/2/

አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሰህ

ስቃይ ያልበገረህ

አ.ዝ

የፈጣሪውን ስም ፍጡነ ረድኤት

ስለመሰከረ

/2/

ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ

የስቃይ መሳርያ ፍጡነ ረድኤት

ያላዘናጋህ

መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተነህ

አ.ዝ

ለእምንቱ ተጋዳይ ፍጡነ ረድኤት

ታማኝ ወታደር

ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር

ስቃይ ቢደርስብህ ፍጡነ ረድኤት

በመታገስህ

ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ

አ.ዝ

ለሰማው ይደንቃል ፍጡነ ረድኤት

ያንተ ሰማዕትነት

ምሳሌ ይሆናል ለሁሉ ፍጥረት

ገድልህ ይናገራል ፍጡነ ረድኤት

ክብር እንደተሰጠህ

ጊዜ የማይሽረው ምግባረ ሀይማኖትህ

አ.ዝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening