ጠቅላላ

General

ሠባቱ ሊቃነ መላዕክት

Lyrics

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

ሠይጣንን ድል ያረግክ በፈጣሪ ኃይል

የኃይላት አለቃ የትህትና መልአክ

እናመስግን አንተን አፎምያን ያዳንክ

ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል

ልደትን ያበሰርክ ለማርያም ድንግል

መልአከ ብስራት/3/ ቅዱስ ገብርኤል

ፈታሄ ማሕፀን ቅዱስ ሩፋኤል

የሰዎችን ችግር ፈጥነህ የምታቀል

ባንተ አማላጅነት ፈጣሪን ስንለምን

ቶሎ ድረስና ረድኤትህን ስጠን

መጋቤ ብርኃናት ቅዱስ ራጉኤል

በምስጋና ትጉህ ቀን ሌሊት ሳትል

ስዕልህ ፊት ቆመን አንተን ስንማፀን

እዘንልንና ገፅህን አብራልን

ቅዱስ ዑራኤል ሊቀመላእክት

ኢትዮጵያን የባረክ በድንግል ስደት

መልአከ ሰላም/2/ በመስቀልህ ባርካት ይህችን ዓለም

ቅዱስ ሩፋኤል ብርኃናዊ መልአክ

ሰማያዊ ህብስት ለድንግል የመገብክ

በነፍስ ጥምና ርሀብ ጠውልገን እንዳንደርቅ

ምልጃህ አይለየን ከሲኦል እንዳንወድቅ

ባሕርና ወንዙ በልክ እንዲሞሉ

ዝናብን የምታሰጥ ለዓለሙ ሁሉ

በኃጢያት እንዳንሞት ፍሬን ሳናፈራ

ቅዱስ ሳቁኤል ሆይ ጠብቀን አደራ

እንፅና ሲል ገብርኤል ባለንበት ቦታ

በሣጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ

ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ

የሣጥናኤል ምኞት እንደ አበባ እረግፎ

ሚካኤል ተሸመ በእምነት ተደግፎ

ሣጥናኤል ወደቀ ፀጋውን ተገፎ

ቅዱሳን መላእክት በእምነት የፀናችሁ

በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ

ስግደት ዘበፀጋ እንስገድላችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening