✦
ጠቅላላ
•General
ሠላም ሠላም
Lyrics
ሠላም ሠላም/2/ የታቦር ተራራ
ሠርሃነ መለኮት በአንቺ ላይ አበራ
ሠላም ሠላም ሠላም ሠላም
ሙሴና ኤልያስ እንዲያ ሲሸበሩ
ምነው አንቺ አልፈራሽ ምንድነው ምሥጢሩ
ደቀ መዛሙርቱ ከሱ ጋር የዋሉ
የአምላክን ድምፅ ሰምተው ለመፅናት አልቻሉ
ደቀ መዛሙርቱ በሀሳብ ሲዋኙ
ይኸው በቅርብ ቀን ምልክት አገኙ
በሀና በኢያቄም በእመቤታችን
ይህችን ቀን ባርክልን መድኃኒታችን
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.