Auto Fetched

Zemarian Collection

ይላል አንደበቴ

ቴዎድሮስ ዮሴፍ
Lyrics

ይላል አንደበቴ

ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው

አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው

ትላንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ

ትልሀለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ

#አዝ

የትላንት ህይወቴን ዞር ብዬ ሳየው

ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው

ወደ እረፍቴ መጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ

ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ /2/

#አዝ

በጥልቁ በረሀ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ

መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ

በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ    ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ /2/

#አዝ

የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል

ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል

ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ

የጌታዬ ሀሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ /2

#አዝ

ትላንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ

የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ

በባህሪው ቅዱስ የሌለው አምሳያ

ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening