✦
Auto Fetched
•Zemarian Collection
የሁሉም አይን
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለLyrics
የሁሉም አይን አንተን ተስፋ አድርጓል
ምህረት ቸርነትህ ይጠባበቃል
ሸክሙ ከብዶል አቅልልልን
ያላንተ ጌታ ሌላ ማን አለን
ያለው ይመስላል ለብሶ ሲያዩት
ላይ ታች እያለ ይዞት ጭንቀት
የልጆቹ እንባ ጩኸት ሰልችቶት
ልመና ገባ ድንገት
አዝ
አሳይተኸን ጌታ አትንሳን
በደል አለብን ይቅር በለን
ወርቅ ብር ላይ ተቀምጠን
እንራባለን ፍቅር አተን
አዝ
እንጨት ለቃሚ ባልቴት ነበረች
በስራ በርታ በድኀነት ያለች
በአኪያ ምክንያት ረሃብ ሆኗል
ወደሞት ልንወርድ ተዘጋጅተናል
ኤሊያስ ውጣ ከኮረብት ፋፋ
ህይወት እንዲነግስ ሞት እንዲጠፋ(፪/2)
የሁሉም አይን አንተን ተስፋ አድርጓል
ምህረት ቸርነትህ ይጠባበቃል
ሸክሙ ከብዶል አቅልልልን
ያላንተ ጌታ ሌላ ማን አለን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.