✦
Auto Fetched
•Zemarian Collection
የልቤን በልቤ ይዤ
ዲ/ን ልዑል ሰገድLyrics
የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጂኝ እላለሁ/2/
አዝ
ግራ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል/2/
አዝ
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ/2/
አዝ
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ/2/
አዝ
አሁንም ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.