Auto Fetched

Zemarian Collection

ይቅር ስላልከኝ

ዘማሪ አቤል መክብብ
Lyrics

✞ ይቅር ስላልከኝ ✞

ይቅር ስላልከኝ ነው የኔ መቆም

ደሞ እንዳልፈርድ እርዳኝ(፪)

በሰዎች ድካም

ለዛሬ መድረሴ አይደል በጽድቄ

እያነሳኸኝ ነው አይተህ ወድቄ

በፈረድኩበት ፍርድ እንዳይፈረድ

አልሁን ፈሪሳዊ ወንድሜን ልውደድ

ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል

አለ በእኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል (፪)

አዝ= = = = =

ባታለብሰኝ ኖሮ ነውሬን ሸፍነህ

ባታቆመኝ ኖሮ በደሌን ከድነህ

በጠፋ ነበር ስም አጠራሬ

ድካሜ ብዙ ነው እንደራስ ፀጉሬ

ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል

አለ በእኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል(፪)

አዝ= = = = =

በምህረትህ ብዛት ከቤትህ ልግባ

ዘወትር ላቅርብልህ የእንባዬ መባ

የውስጤን ማንነት ላንተ ልግለጥ

ከሰው አሳልፈህ ስለማትሰጥ

ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል

አለ በእኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል (፪)

አዝ= = = = =

እለት እለት ግብሬ ኃጢአት መስራት ነው

አንተ እለት እለት እኔን መማር ነው

የበደለን መተው ያንተ ነውና

በወንድሜ መማር ቆሜ አልቅና

ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል

አለ በእኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል /፪/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening